ክርስቲያኖ ሮናልዶ የዓለማችን የምንጊዜም ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ሆነ::

የጁቬንትሱ አጥቂ ክርስቲያኖ ሮናልዶ 760 ጎሎችን በማስቆጠር በእግር ኳስ ታሪክ የዓለማችን የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ መሆን ቻለ፡፡ ሮናልዶ ትናንት ምሽት በጣሊያን ሱፐር ካፕ ናፖሊ ላይ ጎል ማስቆጠሩን ተከትሎ የምንጊዜም ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ክብረ ወሰን ባለቤት ሆኗል፡፡ትናንት ምሽት ያስቆጠረው ጎል 760ኛ ጎሉ ሲሆን፥ ከዚህ ቀደም የኦስትሪያው ዮሴፍ ቢካን ያስቆጠረውን 759 ጎልን አሻሽሎታል፡፡ፖርቹጋላዊው አጥቂ በቅርቡ የብራዚላዊውን ፔሌ የ757 ጎል ክብረ ወሰን መጋራቱ ይታወሳል፡