LatestNewsPolitics

#በትግራይ ልዩ ኃይል ጥቃት ተሰንዝሮባቸው ነበሩ የተባሉና ከጥቃቱ ሸሽተው ወደ ሱዳኗ ገዳሪፍ ግዛት ገብተው የነበሩ 50 የመከላከያ ሰራዊትና የፌዴራል ፖሊስ አባላት ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ተሰምቷል፡፡

በትግራይ ክልል ግጭቱ ከመቀስቀሱ በፊት በማይካድራ ከተማ አቅራቢያ የነበሩት እነዚሁ የመከላከያና የፖሊስ አባላት በትግራይ ልዩ ኃይል እጅ እንዲሰጡ የተጠየቁ ነበሩ፡፡

ይሁንና አባላቱ ወደ ሱዳን በመዝለቅ ሉግዲ በተባለው የድንበር አካባቢ ለሱዳን ባለስልጣናት እጅ መስጠታቸው ተነግሯል፡፡ አሁን የኢትዮጵያ መንግሥትና የሱዳን ባለስልጣናት ባደረጉት ንግግር መከላከያና የፖሊስ አባላቱ ወደ አማራ ክልል መግባታቸውም ታውቋል፡፡#አዲስ_ነገር #Whatsnew_ebs