LatestNews

ዛሬ ምሽት ጁፒተር እና ሳተርን በአንድ ላይ ይገጥማሉ ተባለ

ጁፒተር እና ሳተርን በአንድ ላይ ገጥመው አንድ ፕላኔት መስለው እንደሚታዩ ሳይንቲስቶች ጠቁመዋል።ይህ የጁፒተር እና ሳተርን ጥምረት የሚፈጥረው ብርሃን ዛሬ ምሽት ሊታይ እንደሚችልም ተነግሯል።ክስተቱ ‘ዘ ስታር ኦፍ ቤቴልሄም’ ወይም የቤቴልሄም ኮከብ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ፕላኔቶቹ ከቀን ቀን እየተቀራረቡ መጥተው ዛሬ ምሽት ደማቅ ብርሃን ሊፈነጥቁ ይችላሉ ተብሎ ይጠበቃል።ከ2 ሺህ ዓመታት በፊት ሰማይ ላይ እጅግ ደማቅ ብርሃን ታይቶ እንደነበር የሚናገሩት ሳይንቲስቶች ይህ ክስተት አሁን ሊፈጠር ይችላል ከተባለው ጋር ተመሳሳይነት ሳይኖረው አይቀርም ብለዋል።የአየር ሁኔታው አስተማማኝ አይደለም ያሉት በካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ የአስትሮኖሚ ተቋም ምሁሯ ዶክተር ካሮሊን ክራውፎርድ በደመና መካከል በተገኘ ቀዳዳ ሁለቱ ፕላኔቶች ገጥመው የሚፈጥሩት ብርሃን ሊታይ እንደሚችል ለቢቢሲ ተናግረዋል።