Latest

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ እና የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኮይሻ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብን ጎበኙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኮይሻ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብን ጎበኙ።

ግድቡ በአንድ ጊዜ 2 ሺህ 200 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት የሚችል ሲሆን በዓመት ደግሞ 6 ሺህ ጊጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫል።

የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት አጠቃላይ አፈፃፀም በአሁኑ ወቅት 36 በመቶ የደረሰ ሲሆን ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ ከኃይል ማመንጫነት ባሻገር ለቱሪዝም መዳረሻ እንደሚሆን ይጠበቃል።

በግንባታ ላይ የሚገኘው የኮይሻ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአንድ ወር በፊት መጎብኘታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።