አርሶ አደሩ የደረሱ ሰብሎቹን በፍጥነትና በጥንቃቄ እንዲሰበስብ የግብርና ሚኒስቴር አሳሰበ።

በአገራችን በየዓመቱ ከሚሰበሰበው ምርት ውስጥ ከ25 እስክ 30 በመቶ የሚሆነው ምርት ብክነት እንደሚገጥመው የገለጸው የግብርና ሚኒስቴር ዘንድሮ በምርት ስብሰባ ወቅት ተመሳሳይ ችግር እንዳይከሰት አርሶ አደሩ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት ሲል አሳስቧል፡፡

በዘንድሮ የመኸር ወቅት በዘር ከተሸፈነው 13 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሔክታር የእርሻ መሬት ከ335 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚገኝ የሚታሰብ ሲሆን ከነበረው የዝናብ ሁኔታ አንፃር ደግሞ በምርት ወቅቱ የተሻለ ምርት እንደሚጠበቅ ነው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የገለጸው፡፡