ኢትዮጵያ ለ100 የደቡብ ሱዳን ዶክተሮች ነጻ የትምህርት እድል ሰጠች

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ለ100 የደቡብ ሱዳን የህክምና ዶክተሮች ነጻ የትምህርት እድል መስጠቷን የደቡብ ሱዳን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።ለደቡብ ሱዳናውያኑ ዶክተሮች የተሰጠው ነጻ የትምህርት እድል በትምህርት ዘርፎቻቸው ስፔሻላይዝድ እንዲያደርጉ መሆኑን በሚኒስቴሩ የስልጠና እና ፕሮፌሽናል ልማት ዳይሬክተር ጄኔራል ማይክል ማዲንግ ገልፀዋል።ዳይሬክተር ጄኔራሉ በተለይ ስፔሻላይዝድ ማድረግ ለሚፈልጉ ደቡብ ሱዳውያን ዶክተሮች ነጻ የትምህርት እድል እንደተሰጠ ነው በሰጡት መግለጫ ያስታወቁት።በአሁኑ ወቅት ነፃ የትምህርት እድሉን ማግኘት የሚፈልጉ ዶክተሮች ምዝገባ እየተካሄደ መሆኑን ሱዳን ፓስት በዘገባው አስፍሯል።እንዲሁም ነፃ የትምህርቱን ለማግኘት የመግቢያ ፈተና እደሚሰጥ የተገለፀ ሲሆን ኢትዮጵያም የመግቢያ ፈተናው ያለፉትን ብቻ እንደምትቀበል ተገልጿል።