በህወሃት ታጣቂ ቡድን ከበባ ውስጥ ገብቶ ለ5 ቀናት ካለምግብና ውሀ የቆየው የሰሜን ዕዝ ጦር ከከበባ በመውጣትና ራሱን መልሶ በማደራጀት እያጠቃ ከዳንሻ ጀምሮ በርካታ ቦታዎችን መቆጣጠሩንና ወደፊትም በመገስገስ ላይ መሆኑን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ገልጸዋል።

ጄኔራል ብርሃኑ አክለውም በከበባ ውስጥ ገብቶ የነበረው የሰሜን እዝ ሰራዊት 4ኛ ሜካናይዝድ፣ 5ኛ ሜካናይዝድ 7ኛ ሜካናይዝድ፣ 8ኛ ሜካናይዝድ፣ 11ኛ ክፍለ ጦር፣ 20ኛ ክፍለ ጦር፣ 23ኛ ክፍለ ጦርና 31ኛ ክፍለ ጦር መሆናቸውንም ለኢዜአ ገልጸዋል።

ሰራዊቱን ከከበባ ለማላቀቅ ከምስራቅ፣ ከደቡብና ከምዕራብ ወደስፍራው በመድረስ የሰሜን እዝን ለመታደግ ለቻሉት የሰራዊቱ አመራርና አባላት የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።