የአሜሪካ የደህንነት ተቋማት ዶናልድ ትራምፕ ምርጫው ተጭበርብሯል በሚል ያቀረቡትን ክስ ውድቅ አደረጉት፡፡

የአሜሪካ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የሚመለከታች መስሪያ ቤቶች ባወጡት የጋራ መግለጫ እንዳመለከቱት በቅርቡ የተካሄደው የአሜሪካ ምርጫ ደረጃውን የጠበቀ፣በአሜሪካ ታሪክ እጅግ ደህንነቱ የተጠበቀና ምንም አይነት እንከን የሌለው ነው ብለዋል፡፡

በፕሬዝዳንት ትራምፕ ከ2 ነጥብ 7 ሚሊየን በላይ የመራጮች ድምጽ ጠፍቷል በሚል የቀረበው ቅሬታም ማስረጃ የሌለው ነው በሚል ውድቅ አድርገውታል፡፡