የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለአገር መከላከያ ሰራዊት የሚውል ከ12 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጋቸው ተገልጿል።

ተቋሙ በሀገራዊ ጉዳይ ላይ ከዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ ጋር ውይይት ያካሄደ ሲሆን ሀረማያ፣ ጅማ፣ መቱና ወለጋ ዩኒቨርስቲዎችን ጨምሮ አጠቃልይ ከ6 ዩኒቨርስቲዎች ከ12 ሚሊየን ብር በላይ ገንዝብና የአይነት ድጋፍ እስካሁን ማሰባሰብ መቻሉን አስታውቋል።