#የትግራይ ክልል ዘመቻ ጋር በተያያዘ የፌዴራል መንግስት የሰጠውን የ72 ሰዓት ጊዜ በመጠቀም በርካታ የትግራይ ሚሊሻና ልዩ ኃይል አባላት በየግንባሩ እጅ እየሰጡ መሆናቸውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ማጣሪያ ድረገጽ አስታወቀ፡፡

በገጹ የወጣው መረጃ በተለይም በአፋር ክልል በኩል ብዙዎች ገብተው እጅ የሰጡ መሆኑንና በማይ ጸብሪ ተቆርጦ የቀረው ኃይልም እንዲሁ እጁን በሰላም በመስጠት ላይ መሆኑን ገልጿል፡፡

ጥሪውን ሰምተው እጅ በመስጠት ላይ ለሚገኙ የትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሺያ አባላት ለሕዝባቸው በማሰባቸው መንግሥት ምስጋናውን እንደሚያቀርብ የገለጸው የመረጃ ማጣሪያ ድረገጹ በህወሃት ቡድን ተጽዕኖ ውስጥ ናቸው ላላቸው የትግራይ ልዩ ሃይል አባላት ደግሞ በያላችሁበት ትጥቃችሁን ፈትታችሁና የቡድኑ መጠቀሚያ ከመሆን ተቆጥባችሁ መከላከያ እስከሚደርስላችሁ ጠብቁ ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡#አዲስ_ነገር #Whatsnew_ebs