በቀጣይ ሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ጃንሜዳ ወደ ቀድሞ አገልግሎቱ እንደሚመለስ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አስታወቁ።

ምክትል ከንቲባዋ ዛሬ ማለዳውን ከተለያዩ አካት ጋር በጋራ በመሆን ጃንሜዳን የማጽዳት ዘመቻ አካሄዱ።

በጽዳት ዘመቻውም በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሳቢያ ከፒያሳ ወደ ጃንሜዳ የተዘዋወረውን የአትክልት መገበያያ ስፍራ ሙሉ በሙሉ በማንሳት ለጥምቀት በዓልና ለወጣቶች የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ይመለሳል ያሉት በጃንሜዳ የሚገኙ ነጋዴዎች #ከነገ #ጀምሮ ወደ ሀይሌ ጋርመንት ሙሉ በሙሉ ይሸጋገራሉ ብለዋል፡፡#አዲስ_ነገር #Whatsnew_ebs