ጠ/ሚ ዐቢይ በጤና ሚኒስቴር የሰው ሰራሽ አካል እና የአካል ድጋፍ ማደራጃ ድርጅትን ጎብኝተዋል

 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በጤና ሚኒስቴር የሰው ሰራሽ አካል እና የአካል ድጋፍ ማደራጃ ድርጅትን ጎብኝተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰው ሰራሽ አካል እና የአካል ድጋፍ ማደራጃ ድርጅትን ጉብኝት ያካሄዱት ረፋድ ላይ ነው፡፡

ድርጅቱ ለተጎዱ የመከላከያ ሠራዊት አባላትና ለሲቪሎች ሰው ሠራሽ አካል ይሰራል፡፡

በሕግ ማስከበር ሂደቱና በሌሎችም ጊዜያት የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው በበጎ ፈቃደኞችና በድርጅቱ ባለሞያዎች የሚከናወነውን የሰው ሠራሽ አካል ማምረቻ ድርጅት  ሠራተኞች የሚደነቅ ሥራ እየሠሩ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከውጭ መጥተው በበጎ ፈቃደኝነት ይህንን ታላቅ ሥራ የሚሠሩ ሰሎሞን አማረን የመሰሉ ወገኖች ሊበረታቱ ይገባልም ብለዋል።