የመንግሥታቱ ድርጅት የማይናማር መፈንቅለ መንግሥት አድራጊዎችን አስጠነቀቀ፡፡

የድርጅቱ የማይናማር ልዩ መልእክተኛ ክርስትያን ሽራነር በርነር እንዳሉት መፈንቅለ መንግስት አድራጊዎቹ በሀገሪቱ ዜጎች ላይ የሚወስዱት የጭካኔ ተግባር ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው ነው፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መፈንቅለ-መንግስቱንና በቀድሞዋ ሲቪል መሪ አን ሳን ሱቺ ከስልጣን መውረድ ላይ ተቃውሞ እያቀረቡ ሲሆን የጦር ሀይሉም በተቃዋሚዎች ላይ እርምጃ እየወሰደ ነው፡፡ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት አድራጊዎች ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመዝጋትና በማቆራረጥ ህዝባዊ ተቃውሞውን ለማለሳለስ እየጣሩ እንደሚገኙ የቢቢሲ ዘገባ ያሳያል፡፡#አዲስ_ነገር#Whatsnew_ebs