የእንቁጣጣሽ ሎተሪ 1ኛ ዕጣ አሸናፊ ነኝ የሚል እስካሁን አልተገኘም

የብሔራዊ ሎቶሪ አስተዳደር ጳጉሜ አምስት ቀን 2012 ዓ.ም በወጣው እጣ የ20 ሚሊየን ብር ባለዕድል የሆነው ግለሰብ እስካሁን መጥቶ ገንዘቡን አልተረከበኝም አለ፡፡ አስተዳደሩ በአዲስ መልክ ለሁለት ተከታታይ ጊዜ የ20 ሚሊየን ብር እጣ አዘጋጅቶ ማቅረቡ የሚታወስ ሲሆን ለሁለተኛ ጊዜ የእጣ ቁጥሩን ካወጣ ከአምስት ወራቶች በላይ ቢሆንም የ1ኛ እጣ ሽልማቱን የወሰደ ግለሰብ እስካሁን አለመኖሩን እወቁልኝ ብሏል፡፡ለመጀመሪያ ጊዜ አቅርቦት የነበረው 20 ሚሊየን ብር የሚያሸልመው እጣ በጊዜው ለአሸናፊው ማስረከቡንም አስተዳደሩ ያስታወቀ ሲሆን ጳጉሜ አምስት ቀን 2012 ዓ.ም የወጣው የ20 ሚሊየን ብር አሸናፊ የእጣ ቁጥር 02 16 884 እንደነበረም የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር አስታውሷል፡፡ ታዲያ የሎተሪው አሸናፊ እስከ መጋቢት አንድ ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ብቻ ከመጣ ገንዘቡን መውሰድ ይችላልም ብሏል፡፡