የእጩዎች ምዝገባን ዘግይተው በጀመሩ ቦታዎች ምዝገባው እስከ የካቲት 30 መራዘሙን ምርጫ ቦርድ አስታወቀ

የእጩዎች ምዝገባን ዘግይተው በጀመሩ ቦታዎች ምዝገባው እስከ የካቲት 30 መራዘሙን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። ምርጫ ቦርዱ በመጀመሪያ ዙር እጩዎች ምዝገባ የተጀመረባቸው ክልልሎችና የከተማ መስተዳድሮች ማለትም#በአዲስ አበባ፣ #በድሬዳዋ#በኦሮሚያ#በሃረሪ#በጋምቤላንና#በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የእጩዎች ምዝገባ በትላንትናው እለት መጠናቀቁን አስታውቋል። በተመሳሳይ #በአማራ#በሶማሌ#በአፋር#በምእራብና ምስራቅ ወለጋ ዞን ኦሮሚያ፣ #በደ/ብ/ብ/ህዝብና #በሲዳማ በቢሮዎች መከፈት መዘግየት የተነሳ፣ የትራንስፓርትና ሌሎች እክሎችን እንዲሁም የፓርቲዎች አቤቱታዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት በሁለተኛ ዙር የእጩዎች ምዝገባ እስከ #የካቲት 30/2013 ዓ.ም ድረስ መራዘሙን በይፋዊ ማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል። ፓርቲዎች በተሰጡት ተጨማሪ ቀናት ውስጥ ምዝገባቸውን አንዲያጠናቅቁም ምርጫ ቦርዱ አሳስቧል።

#አዲስ_ነገር#Whatsnew_ebs