በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ክትባት ቅዳሜ መሰጠት ይጀምራል

#በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ ክትባት ከሚመጣው ቅዳሜ ጀምሮ መሰጠት ይጀምራል ተባለ።የጤና ሚኒስቴር በማህበራዊ ትስስር ገጽ ባወጣው መረጃ እንዳመለከተው ከሆነ ክትባቱን ለመጀመር የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅቶችን በስፋት እያከናንኩ ነው ያለ ሲሆን በዚህም ስልጠናዎችን መስጠት፣ ክትባቱን ማሰራጨትና ክትባቱን መውሰድ የሚገባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች የመለየት ተግባርና ሌሎችም ዝግጅቶች በስፋት መከናወናቸውን አመልክቷ፤። በመጪው ቅዳሜ መጋቢት 4/2013 ዓ.ም በኢትዮጵያ በሁሉም ክልሎችና የከተማ መስተዳድሮች በተገኙበት የኮቪድ-19 ክትባት የመስጠቱ መርኃ ግብር እንደሚጀመርም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

#አዲስ_ነገር#Whatsnew_ebs