የሸገር ዳቦ ፋብሪካ ከዛሬ ጀምሮ በቀን 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ዳቦ ያመርታል

ሸገር ዳቦ ፋብሪካ በሙሉ አቅሙ ወደ ማምረት ሊገባ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተመራ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ቡድን ፋብሪካ ያለበትን አጠቃላይ ሁኔታ ጎብኝቷል፡፡

በዚህ ወቅትም ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዳቦ ፋብሪካው በዚህ ሳምንት ሙሉ በሙሉ ወደ ማምረት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ለዚህም የከተማ አስተዳደሩ በወር 100 ሺህ ኩንታል ስንዴ እንደሚያቀርብም ነው የተናገሩት፡፡

የሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አቶ ጀማል አህመድ ፋብሪካው በቀን 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ዳቦ ማምረት ይጀምራል ብለዋል፡፡