ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በወንጪ የሚገነባው የገበታ ለአገር ፕሮጀክትን አስጀመሩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከገበታ ለአገር አንዱ የሆነውን የወንጪ ፕሮጀክት ግንባታን በይፋ አስጀምረዋል፡፡በወንጪ የሚገነባው የገበታ ለአገር ፕሮጀክት በተለያየ ምዕራፍ የሚገነባ ሲሆን፣ ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያስጀመሩት የወንጪ – ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም ፕሮጀክት አካል የሆነውና ወደ ሀይቆች የሚሄዱት መንገዶች እና አጠቃላይ በተራራው ዙሪያ ያሉ የአስፓልት መንገዶችን ግንባታ መሆኑ ተገልጿል፡፡ በሂደት ሀይቆችን ማልማትን ጨምሮ አነስተኛ አውሮፕላን ማረፊያ ፣ ጤና ጣቢያዎች፣ የቴሌኮም እና የመብራት አገልግሎቶች በመንግስትና በባለሀብቶች የሚገነቡ የቱሪዝም መዳረሻዎች የሚገነቡለት ይሆናል ተብሏል፡ በፕሮጀክቱ ማስጀመሪያ ስነ ስርዓት ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የፌዴራልና የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡