የኤርትራ ወታደሮች የኢትዮጵያን ድንበር ለቀው እንዲወጡ ከስምምነት ላይ መደረሱን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከሰሞኑ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የቀረቡላቸውን ጥያቄዎች ተንተርሰው በሰጡት ሰፋ ያለ ምላሽና ማብራሪያ የኤርትራ ወታደሮችን ወደ ኢትዮጵያ ድንበር የመግባት ጉዳይ እውነታነት በይፋ መናገራቸው ይታወሳል፡፡ ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ታዲያ ወደ አገራችን ድንበር የዘለቁት የኤርትራ ወታደሮች የኢትዮጵያን ድንበር ለቀው እንዲወጡ ከስምምነት ላይ መደረሱን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሳውቀዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሳወቁት ትላንት ከሰዓት በኋላ ወደ አስመራ ካቀኑ በኋላ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ በለጠፉት መረጃ ሲሆን በጽሁፋቸውም በህውሃት ቡድን የሮኬት ተኳሽነት የደህንነት ስጋት ኤርትራ ወታደሮቿን ወደኢትዮጵያ ድንበር ማስገባቷን ጠቅሰው አሁን ግን በአፋጣኝ ከኢትዮጵያ ድንበር እንዲወጡና ቦታውም በኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር እንዲሆን መወሰኑን ገልጸዋል፡፡ልዑኩ በኤርትራ የነበረውን የሁለት ቀናት ጉብኝቱን አጠናቆ ተመልሷል ::

#አዲስ_ነገር#Whatsnew_ebs