የኢትዮጵያ የግብፅ እና የሱዳን ሚኒስትሮች የፊታችን ቅዳሜ በኮንጎ ኪንሻሳ ድርድር እንደሚያካሂዱ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ግብፅና ሱዳን ሚኒስትሮች የፊታችን ቅዳሜ በኮንጎ ኪንሻሳ ተገናኝተው ለሦስት ቀናት የሚዘልቅ የህዳሴ ግድብ ድርድር እንደሚያካሂዱ ተገለጸ፡፡ስብሰባውን የሚመሩትም የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ፕሬዝዳንት ፊሊክስ ቲሺኬዲ ሲሆኑ የስብሰባውን መካሄድ ማረጋገጫ የሰጠውም የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደሆነ እንዲሁም በስብሰባው ላይ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህመትም እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡ሱዳንና ግብፅ ከአፍሪካ ህብረት በተጨማሪ አሜሪካ፣ የአውሮፓ ህብረት እንዲሁም የዓለም ባንክ በድርድሩ ይሳተፉ የሚል አቋም ሲያራምዱ ቆይተዋል፡፡ኢትዮጵያ በበኩሏ የድርድሩ አካሄድ የሚቀየረው በካርቱም የመርህ ስምምነት መሰረት ሦስቱም ተደራዳሪ ሀገራት ሲስማሙ እንጂ በሀገራት የተናጠል ፍላጎት እንዳልሆነ እየገለጸች ትገኛለች፡፡

#አዲስ_ነገር#Whatsnew_ebs