የአፍሪካን ያለፉትን 500 ዓመታት ትክክለኛ ታሪክ የያዘ ነው የተባለለትን አፍሪካን ፋክት ቡክ መጽሃፍ የዚምባብዌ ልዑክ ለኢትዮጵያ አስረክቧል፡፡

የአፍሪካን ያለፉትን 500 ዓመታት ትክክለኛ ታሪክ የያዘ ነው የተባለለትን አፍሪካን ፋክት ቡክ መጽሃፍ የዚምባብዌ ልዑክ ለኢትዮጵያ አስረክቧል፡፡በዚምባብዌ ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ የተላከው ልዑክ መጽሃፉን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ያስረከበ ሲሆን የአፍሪካ ሕብረት ያለፉት 500 ዓመታት የአፍሪካ ትክክለኛው ታሪክ እንዲመዘገብ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት መዘጋጀቱም በዚሁ ጊዜ ተነግሯል፡፡የህብረቱ የአጀንዳ 2063 ጠቃሚ አካል ነው የተባለው ይህ መጽሃፍ የእውነታዎች ስብስብ፣ የአፍሪካን ባህል፣ ታሪክና ትውፊት ለዓለም የሚያስተዋውቅ እንደሆነም ተገልጿል፡፡መጽሃፉን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ያስረከበው ልዑክ ቡድኑ ይህንን መጽሐፍ በማበርከት ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ነጻነት የተጫወተችውን ሚናና ለፓን-አፍሪካዊነት የምታደርገውን ቀጣይ ድጋፍ በማድነቅ ዕውቅና መስጠቱን ጨምሮ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ያመለከተው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ነው።

#አዲስ_ነገር#Whatsnew_ebs