የአማጽያን ጥቃት በበረታባት ቻድ ፕሬዝዳንት ኢድሪስ ዴቢ በምርጫ ማሸነፋቸውን ተናገሩ፡፡

የአማጽያን ጥቃት በበረታባት ቻድ ፕሬዝዳንት ኢድሪስ ዴቢ በምርጫ ማሸነፋቸውን ተናገሩ፡፡ፕሬዝዳንት ዴቢ እስካሁን ለ30 አመት በስልጣን ላይ የቆዩ ሲሆን አሁን እንደገና ተመረጡ ሲባል ለስድስተኛ ጊዜ ነው፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው ፕሬዝዳንቱ እስካሁን በተካሄደው የምርጫው ጊዜያዊ ውጤት የ80 ከመቶውን መራጭ ድምጽ አግኝተዋል፡፡የኢድሪስ ዴቢ ደጋፊዎች በመዲናዋ ኢንጃሚና ደስታቸውን እየገለጹ ሲሆን ሰሞኑን ጥቃት የጀመሩት አማጽያን ከመንግስት ሀይሎች ጋር እየተፋለሙ ነው፡፡ እንዳውም አማጽያኑ ወደ መዲናዋ እየተጠጉ ነው በመባሉ እንደ አሜሪካና ብሪታንያ ያሉ ሀገራት ዜጎቻቸውን ከሀገሪቱ እያስወጡ ነው፡፡ በሌላ በኩል ግን የፕሬዝዳንቱ ስደስተኛው የምርጫ ድል ብስራት በተገለጸበት ወቅት አማጽያኑም ሽንፈት እየደረሰባቸው መሆኑ በባለስልጣናት ተገልጿል፡፡

#አዲስ_ነገር #Whatsnew_ebs