በትግራይ ክልል በሁለት ዙር የ4 ነጥብ 5 ሚሊዮንና የ2 ነጥብ 9 ሚሊዮን ሰዎችን ፍላጎት ያገናዘበ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ተከናውኗል፡፡

በትግራይ ክልል በሁለት ዙር የ4 ነጥብ 5 ሚሊዮንና የ2 ነጥብ 9 ሚሊዮን ሰዎችን ፍላጎት ያገናዘበ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት መከናወኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን አስታውቀዋል። አቶ ደመቀ መኮንን ይህንን ያስታወቁት ከእንግሊዝ የረሀብ መከላከልና ሰብዓዊ ጉዳዮች ልዩ መልዕክተኛ ጋር በተወያዩበት ወቅት ሲሆን በክልሉ ሦስተኛው ዙር የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦትም ከወዲሁ እየተካሄደ መሆኑን አያይዘው ገልጸዋል። በተጨማሪም መንግስት የተፈናቃዮችን ፍላጎት ለማሟላትና በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶችን ተደራሽነት ለማስፋት እያደረገ ነው ስላሉት ጥረትም እንዲሁ አብራርተዋል። ከሰብዓዊ ድጋፉ ባለፈ በክልሉ ተፈጽመዋል ስለተባሉ ኢሰብዓዊ ድርጊቶችም የተባበሩት መንግስታት፣ የአፍሪካ ህብረትና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽንን ጨምሮ የተለያዩ አካላት ጉዳዩን ለማጣራት እየሰሩ መሆኑን አንስተዋል። መረጃውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ነው ያገኘው፡፡