የሐዋሳ ኢንደስትሪያል ፓርክ በ11 ወራት ብቻ 114 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ማስገባቱ ተነገረ።

የሐዋሳ ኢንደስትሪያል ፓርክ በ2013 ዓ.ም በ11 ወራት ብቻ 114 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ማስገባቱ ተነገረ። ፓርኩ የውጪ ምንዛሪ ከማስገባቱ በተጨማሪ ለ35 ሺህ ሰዎች ቀጥተኛ የስራ እድል መፍጠሩ የተገለጸ ሲሆን ለእነዚሁ ሰራተኞች የመኖሪያ የቤት እጥረት እንዳይገጥማቸው በፓርኩ ውስጥ መሬት በማዘጋጀት 7 የመኖሪያ አፓርታማዎች ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ እንደሆነ ተገልጿል። በፓርኩ ውስጥ 52 የፍብሪካ ሸዶች እንዳሉ የተገረ ሲሆን በእነዚህ ሸዶች ውስጥም 3 ኢትዮጵያዊያን ባለሐብቶችን ጨምሮ የተለያዩ የውጭ አገራት ባለሐብቶች ገብተው በመስራት ላይ ይገኛሉ ተብሏል። ባለሐብቶቹም በጨርቃጨርቅ ማምረትና በመስፋት ላይ እንደሆኑና ምርቶቻቸውን ሙሉ ለሙሉ ለውጪ ገበያ እንደሚያቀርቡ ተገልጿል። ፓርኩ የውጪ ምንዛሬ ለአገሪቱ ከማስገኘቱና ለበርካታ ሰዎች የስራ እድል ከመፍጠሩ ባሻገር የቴክኖሎጂ ሽግግር በማምጣት ረገድ አሁን ላይ በውጭ ዜጎች ተይዘው የነበሩ ስራዎች በኢትዮጵያን እንደተሸፈነ ሰምተናል።የሐዋሳ ኢንዱስሪያል ፓርክ ፓርኩ በ11 ወራት ብቻ 114 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ማስገባቱ ተነገረ::