ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት አመራሮች ህጻናትን በጉዲፈቻነት ለማሳደግ ተረከቡ።

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የካቢኔ አባላት እና የተለያዩ ተቋማት አመራሮች “አንድ ቤተሰብ ለአንድ ህጻን” በሚል 306 ህጻናትን በጉዲፈቻነት ለማሳደግ ከአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች እና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ተረከቡ።የዘንድሮውን የክረምት ወራት በጎፍቃድ አገልግሎት 100 ህጻናትን በጉዲፈቻ ፣ባሉበት ሆነው ለማድረግ እና በሌሎች አማራጮች ድጋፍ ለማድረግ እቅድ መያዙን የገለጹት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከፍተኛ አመራሮች ፣የሴክተር ተቋማት እና ባለሀብቶች በጠቅላላው 306 ህጻናት በጉዲፈቻነት ወላጅ እንዲያገኙ ተደርጓል ብለዋል።የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች እና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሃዳስ ኪዱ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ቢሮው በአጠቃላይ 1 ሺ 350 ህጻናት በሀገር ውስጥ እና በውጪ ሀገራት የጉዲፈቻ አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉን ገልጸዋል ።