አጫጭር የኢቢኤስ ስፖርት መረጃዎች

  • በአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ጨዋታዎች የተለየ ነገር ለማሳየት እንደሚሞክሩ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ተናገሩ:: በእርግጠኝነት የምነግራችሁ ነገር እንደ ትናንቱ በፍራቻ አይደለም የምንጫወተው። ከዚህ ቀደም ባልተለመደ መልኩ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ላይ በርከት ያሉ ግቦችን እያገባን በጥሩ አጨዋወት ስንጫወት ነበር። ስለዚህ በቀጣይም ይህ ይቀጥላል። ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
  • የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የፊታችን ሀሙስ ከሴራሊዮን አቻው ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታውን ያደርጋል፡፡ ባለፉት ሳምንታት ለዝግጅት በአዳማ የከተመው ዋልያው ለዚህ ጨዋታ ወደ ባህር ዳር ማቅናቱ ተሰምቷል፡፡ ቡድኑ ለጋና እና ዚምቧቤ ጨዋታ ይረዳው ዘንድም የፊታችን ሀሙስ በ10 ሰዓት ሴራሊዮንን በባህርዳር ኢንተርናሽናል ስቴዲየም ይገጥማል፡፡
  • በግብጽ ሊግ ደማቅ ጊዚን እያሳለፈ የሚገኘው ኢትዮጵያዊው ኮከብ ሽመልስ በቀለ ከቀናቶች በኋላ ዋልያዎቹን ይቀላቀላል፡፡ በምስር አልማካሳ የተሳካ የውድድር አመትን አሳልፎ ለክለቡ 11 ግቦች ከመረብ ያወዳጀው ጨዋታ አቀጣጣዩ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከፊቱ ላሉበት የአለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች በመጪው ሳምንት ወደ አዲስ አበባ እንደሚገባ ተረጋግጧል፡፡
  • የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን የፊታችን ሀሙስ በይፋ ዝግጅቱን ይጀምራል፡፡ ኮስታሪካ ላይ በሚደረገው የወጣቶች የአለም ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ በቅድመ ማጣሪያ እየተሳተፈ የሚገኘው ቡድኑ በወርሃ መስከረም ከሩዋንዳ አቻው ጋር የደርሶ መልስ ጨዋታውን ያደርጋል፡፡ ለዚህም ከፊታችን ሀሙስ አንስቶ በካፍ የልዕቀት ማዕከል ልምምዱን የሚጀምር ይሆናል፡፡
  • የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን ዘመናዊ ጅምናዚየምና እና መዝናኛ ማዕከል አስገንብቶ አስመርቋል። የስፖርትና የመዝናኛ ማዕከሉም ለተቋሙ ሰራተኞቹ የሚሆን የአካል ብቃትና እንቅስቃሴ ማድረጊያ መሆኑም ታውቋል። በምረቃው ስነስርዓት የከተማዉ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
  • የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ለፔር ኤምሪክ ኦባሚያንግ ዝውውር የሚቀርብለትን ጥያቄ ለማድመጥ ዝግጁ መሆኑን ዴይሊ ቴሌግራፍ ዘግቧል፡፡ ባለፉት አመታት የአርሰናል ወሳኝ ሰው ሆኖ ከሀምሳ በላይ የሊግ ግቦችን ከመረብ ያስታረቀውን ጋቦናዊ መንገድ ላለመቆምም አርሰናል በዝውውር መስኮቱ መገባደጃ ተጫዋቹን ለፈላጊ ክለቦቹ አሳልፎ ለመስጠት እቅድ ነድፏል፡፡
  • የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ አሸናፊዎቹ ቼልሲዎች ሳኡል ኑጌዝን እና ጁሊየስ ኮንዴስን ወደ ስታምፎርድ ብሪጅ ለማምጣት እየጣሩ ነው፡፡ የተትረፈረፈ ስብስብ ይዘው ሊጉን በድል ታጅበው የጀመሩት ሰማያዊዎቹ ከአትሌቲኮ ማድሪድ በውሰት ሳኡል ኑጌዝን ለማምጣት እንዲሁም ጂሊየን ኮንዴስን ደግሞ ከሲቪያ ለማዛወር መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ መጀመራቸው ከወደ እንግሊዝ ተነግሯል፡፡
  • በአውሮፓ ታላላቅ ሊግ ጨዋታዎች ዌስትሃም ዩናይትድ ኤስ ሚላን እና ሲቪያ ድል ቀንቷቸዋል፡፡ በለንደን ኦሎምፒክ ስቴዲየም ሌስተር ሲቲን የገጠመው ዌስትሃም ዩናይትድ 4-1 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል፡፡ በላሊጋው ሲቪያ በኤሪክ ላሜላ ብቸኛ ግብ ሄታፌን 1-0 አሸንፏል፡፡ በሴሪያው ኤስ ሚላን ወደ ሉጂ ፌራሪ አቅንቶ በቤራሂም ዲያዝ ግብ ሳምዶሪያን 1-0 ረቷል፡፡
  • የካራባኦ ካፕ ሁለተኛ ዙር ጨዋታዎች የፊታችን ረቡዕ ምሽት ቀጥለው ይደረጋሉ፡፡ የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናልም ወደ ሃውትሮንስ አቅንቶ ምሽት 4፡00 ዌስትብሮሚች አልቢዮን ይገጥማል፡፡ በሌሎች ጨዋታዎች ኒውካስል ዩናይትድ በሜዳው ሴይንት ጀምስ ፓርክ በርንሌይ ሲገጥም ኒውፖርት ካውንቲ ከሳውዝ አምፕተን ይገናኛሉ፡፡

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 7696 ላይ ይላኩልን።

Join Our Telegram

Click Here To follow Us