የነሐሴ 25 የኢቢኤስ ስፖርት አጫጭር መረጃዎች

  • የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የአለም ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታውን ለማድረግ ጋና ደርሷል፡፡ ዋልያው 23 ተጫዋቾችን ጨምሮ ሌሎች ልዑካንን በማካተት ወደ ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገረ ዛሬ ጠዋት ያመራ ሲሆን የፊታችን አርብ ምሽት 1 ሰዓት በኬፕ ኮስት ስቴዲየም በኳታሩ የአለም ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ የጋና አቻውን የሚገጥም ይሆናል፡፡
  • በአፍሪካ ዋንጫው ዝቅተኛ ግምት እንደሚሰጠን ብናውቅም ወደ ውድደሩ ስፍራ የምናመራው አንድ ደረጃ ከፍ ለማለትና ክስተት ለመሆን ነው” ሲል አስቻለው ታመነ ተናገረ ፡ የብሄራዊ ቡድኑ ሁለተኛ አምበል ከሀትሪክ ስፖርት ጋር በነበረው ቆይታ ወደ ውድድሩ ስፍራ የምናመራው በደቡብ አፍሪካ ከነበረን ተሳትፎ አንድ ደረጃ ወደላይ ከፍ ከማለት ባሻገር የውድድሩ ክስተትም ለመሆን ነውና ያን እልማችንን እናሳካለን፡፡ ሲል ተናግሯል፡፡
  • በሴቶች የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ውድድር ተሳታፊ ለመሆን በሴካፋ ዞን የማጣሪያ ውድድራቸውን እያደረጉ የሚገኙት ኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች ሁለተኛ የምድብ ጨዋታቸውን ረቡዕ ያደርጋሉ፡፡ የኬንያውን ቪህጋ ኪውንስን በመርታት ጅማሮዋቸውን ያሳመሩት እንስቶቹ በካራሳኒ ስቴዲየም ረቡዕ በ7 ሰዓት የዛንዚባሩ ክለብ ኒውጄኔሬሽን የሚያገኙ ይሆናል፡፡
  • ለሀገሬ ክብር መስራቴ ደስ አሰኝቶኛል ስትል የፓራ ኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳልያ ባለቤቷ ትህግስት ገዛሕኝ ተናገረች፡፡ በቲ13 የ1500 ሜትር ውድድር አሸናፊዋ ከቢቢሲ ጋር ባደረገችው ቆይታም ይህ ነው ብዮ መናገር አልችልም ፡፡ በጣም ተደስቻለው ከሚኒማ ሟማያ ውጪ በፓራኦሎምፒክ አለም አቀፍ ውድድር ላይ ስሳተፍ የመጀመሪያዪ ነው ፡ ለኢትዮጵያ ክብር በመስራቴ ኩራት ይሰማኛል ስትል ተደምጣለች፡፡
  • የስፖርት ዞን የአመቱ ምርጦች የእውቅና እና ሽልማት ስነ ስርዓት ተካሂዷል፡፡ በተለያዩ ዘርፎች በተካሄደው የሽልማት ስነ ስርዓትም የአመቱ ምርጥ ተጫዋችነት ክብርን አቡበከር ነስሩ አግኝቷል፡ ሚኬል ሳማኪ የአመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ ሲሰኝ ቸርነት ጉግሳ የአመቱ ምርጥ ወጣት ተጫዋች ክብርን ተቀዳጅቷል፡፡ የፋሲል ከነማው ስዩም ከበደ ደግሞ የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝነት ሽልማትን ማግኘት ችሏል፡፡
  • ክርስትያኖ ሮናልዶ በይፋ የማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋች ሆኖ ለመጪዎቹ ሁለት የውድድር አመታት በክለቡ የሚያቀየውን ፊርማ አኑሯል፡፡ ከ12 አመታት በኀላ ወደ ቲያትር ኦፍ ድሪምስ የተመለሰው የ5 ጊዚ የባላንዶር አሸናፊው ሁሉንም ደጋፊዎች እንደገና ለማየት ጓጉቻለው ከፊታችንም ውጤታማ የውድድር ዘመን ይጠብቀናል ሲል ከውል ስምምነቱ በህዋላ ተናግሯል፡፡
  • ሪያል ማድሪድ ማንችስተር ዩናይትድ እና ፓሪሴንት ጀርሜይንን በመርታት የ18አመቱን የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ኤድዋርዶ ካማቪንጋን የግሉ አድርጓል፡፡ ስሙ በስፋት ከአውሮፓ ሃያላኑ ጋር ሲነሳ የከረመው ፈረንሳዊው በመጨረሻም የሎስ ብላንኮሶቹ ንብረት ሆኗል፡፡ ተስፈኛውን ኮከብ ለማስኮብለልም ሪያል ማድሪድ 31 ሚሊየን ዩሮ ፈሰስ አድርጓል፡፡
  • የጣሊያኑ ክለብ ጁቬንቱስ ለክርስትያኖ ሮናልዶ ተተኪ ሞይስ ኪንን ወደ ቱሪን ማምጣቱ እርግጥ ሆኗል፡፡ የ36 አመቱን ፖርቱጋላዊ ክለቡን ከለቀቀ በኋላ ፊት መስመሩ ያለተተኪ የከረመባቸው ቢያንኮሪያዎቹ ከኤቨርተን በሁለት አመት የውሰት ውል የቀድሞ አጥቂያቸውን ሞይስ ኪንን ማስፈረማቸውን አሳውቀዋል፡፡
  • ብራዚላዊው አማካይ ዊልያን ከአርሰናል ጋር መለያየቱ እርግጥ ሆኗል፡፡ ደካሚ ሊባል የሚችል የውድድር አመት በመድፈኞቹ ቤት ያሳለፈው የቀድሞ የቼልሲ ኮከብ የሰሜን ለንደኑን ክለብ ለቆ ወደ ብራዚሉ ኮረንቲያስ ለማምራት ተስማምቷል፡፡ በአርሰናል ቤት ሁለት አመት ቀሪ ኮንትራት የነበረው ዊሊያን ክለቡን በስምምነት መልቀቁን ተከትሎ መድፈኞቹን ከ20 ሚሊየን ፓውንድ ኪሳራም ታድጓል፡፡
  • እንግሊዛዊው አማካይ ጆርዳን ሄንደርን ከሊቨርፑል ጋር ለመጪዎቹ የውድድር አመታት የሚያቆየውን የውል ማራዘሚያ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡ ቀዩቹን በአምበልነት እየመራ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ እና የእንግሊዝ ፕሪሚር ሊግ ዋንጫን ያነሳው የ31 አመቱ አማካይ በአንፊልድ እስከ 2025 የሚያቀየውን የውል ስምምነት ፈርሟል፡፡