የፕሮፌሰር መስፍን ወልድደማሪያም ፋውንዴሽን በይፋ ተመሰረተ፡፡

ፋውንዴሽኑ መምህር ተመራማሪ የሰብአዊ መብት ተሟጋች እንዲሁም ደራሲ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በህይወት ዘመን ላበረከቱት አስተዋጽኦ እንዲሁም ራእያቸውን ለማስቀጠል መመስረቱ ተንግሯል፡፡

የፋውንዴሽኑ የቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ ፋውንዴሽኑን መመስረት ያስፈለግው የሰብዓዊ መብት መከበር ትግል እንዳይደበዝዝ ፣ እንዳይገፈፍ ለማድረግ ነው ብለዋል። ለወጣቶች እንዲደርስ ፣ በጎልማሶች እንዳይዘነጋ፣ ለእውነት የቆሙ ለጭቆና ያልተበገሩ፤ ለምን ? ብለን የምንጠይቅ ሰዎች እስካለን ድረስ መስፍን ወልደማርያም የሰብዓዊ መብት መከበር ፣ የፀረ ጭቆና ግፍ ማህተም ሆኖ ይኖራል ሲሉም አክለዋል።

የፕሮፌሰር መስፍን ልጅ ዶ/ር መቅደስ መስፍን በበኩላቸው የተመሰረተውን ፋውንዴሽን ወደትልቅ ደረጃ ለማድረስ በመተጋጋገዝ እንደሚሰራም ገልፀዋል።
በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በአዲስ አበባ ዋና መስሪያ ቤት የሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሹን በፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ስም እንደሚሰይም ኮሚሽነሩ ዶ/ር ዳንኤል በቀለ አሳውቀዋል።

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ፋውንዴሽን ከመንግስት ፣ ከማንኛውም ሃይማኖት፣ ከጎሳ እንዲሁም የፖለቲካ አመለካከት ገለልተኛ ሆኖ መቋቋሙን በፋውንዴሽኑ ምስረታ ማብሰሪያ መርሃ ግብር ላይ ተገልጿል።ዘገባው የሪፖርተራችን ዓለማየሁ አድማሱ ነው፡፡

Join Our Telegram

Click Here To follow Us