የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ..

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ የምታካሄድውን የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ መጀመሯን አስታወቀች።ቤተ ክርስቲያኒቱ ጥቅምት በገባ በ12ኛው ቀን በምታካሂደው ዓመታዊ ጉባኤዋ የተሰሩ መንፈሳዊ አገልግሎቶችንና አስተምህሮቶችን በመገምገም ማስተካከያ የሚሹ ጉዳዮች ላይ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ይወያያሉ ተብሏል።ይህንኑ ዓመታዊ የቅዱስ ሲኖዶሱን ጉባኤ አስመልክተው መግለጫ የሰጡት አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ከእግዚአብሔር የተሰጠን ቃል የሰውን ሕሊና የሚረታና የሚያሳምን በመሆኑ በብቃት እያስተማርን መሆናችንንና አለመሆናችንን የሚመሰክረው በምድር ላይ ያለው እውነታ ነው ብለዋል።ፓትርያርኩ አክለውም አሁን በአገራችን ላይ እየደረሰ ያለው ከባድ ጉዳት እንዲያበቃ ተግተን መጸለይ ይገባናል ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል።ከጦርነቱ ጋር በታያያዘ የተጎዱ ወገኖች ተደራራቢ ችግር እያጋጠማቸው በመሆኑ ምእመናን በማስተባባር ልንረዳቸውና ልንደርስላቸው ይገባልም በማለት ፓትርያርኩ ጉባኤውን በጸሎት ከፍተው አስጀምረዋል። ዜናው የሪፖርተራችን ፍስሐ ደሳለኝ ነው።

Join Our Telegram

Click Here To follow Us