ካፎር አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬን የበጎ ፈቃድ አምባሳደር አድርጎ ሰየመ ::

ተቀማጭነቱን በአዲስ አበባ ያደረገው ካፎር አፍሪካዊ ግብረ ሰናይ ድርጅት አርቲስት እና የማስታወቂያ ባለሙያ የሆነው ሰራዊት ፍቅሬን የበጎ ፈቃድ አምባሳደር አድርጎ ሰየመ ::ድርጅቱ አርቲስት ሠራዊት ታዋቂ የሚዲያ ሰውነት እንዲሁም የረጅም ጊዜ የስራ ልምዱን በመጠቀም ድርጅቱ ሰለሚሰራቸው ስራዎች በሰዎች ዘንድ ግንዛቤ እንዲኖር በማሰብ እንደመረጠውም አሳውቋል፡፡ካፎር ለዚሁ ስራው በ2022 የአውሮፓዊያን የዘመን ቀመር 20 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ከአጋር አካላቱ የማሰባሰብ እቅድ እንዳለው ተነግሯል ::የድርጅቱ የበጎ ፈቃድ አምባሳደር የተቀበለው አርቲስትና ማስታወቂያ ባለሙያ ሰራዊት ፍቅሬም ከዚህ እቅድ ውስጥ 5 ሚሊዮን ዶላሩን እንዲያሰባስብ የቤት ስራ የተሰጠው ሲሆን ቀሪው ገንዘብ ከሌሎች ምንጮች የሚሰበሰብ ይሆናል ተብሏል፡፡ዜናው የሪፖርተራችን አቤል አበበ ነው፡፡ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 7696 ላይ ይላኩልን።