ተጨማሪ ተጫዋቾች ብሔራዊ ቡድኑን እንዲቀላቀሉ ተወሰነ።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ 3 ተጨማሪ ተጫዋቾች ብሔራዊ ቡድኑን እንዲቀላቀሉ ወስኗል።ብሔራዊ ቡድኑ ባሳለፍነው ረቡዕ ለ25 ተጫዋቾች ጥሪ ማቅረቡ የሚታወስ ሲሆን ትላንት ምሽት በወጣው መረጃም በተጠባባቂነት ተይዘው የነበሩት #ሱራፌል ዳኛቸው ፣ #ፍሬው ጌታሁን እና #ይሁን እንደሻው ብሔራዊ ቡድኑን ተቀላቅለው ወደ ካሜሩን እንዲሄዱ ተወስኗል። በዚህም መሰረት ዋልያው 28 ተጫዋቾችን ይዞ ወደ ስፍራው የሚያቀና ይሆናል።የአህጉሪቱ የእግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ካፍ ብሄራዊ ቡድኖች በዘንድሮ የአፍሪካ ዋንጫ 28 ተጫዋቾችን በቡድናቸው ማካተት እንድሚችሉ ቀደም ብሎ ማስታወቁ የሚታወስ ነው፡፡ምንጭ፦ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 7696 ላይ ይላኩልን።

Telegram: https://t.me/ebstvworldwide

Follow us on: https://linktr.ee/ebstelevision

#ኢቢኤስ