አዲስ የዲያስፖራ ማእከል የተሰኘ በመስቀል አደባባይ ተከፈተ።

ወደ አገር ቤት እየገቡ ላሉ ዲያስፖራዎች በአንድ ማዕከል ሁሉንም የመንግስት አገልግሎቶች የሚያገኙበት አዲስ የዲያስፖራ ማእከል የተሰኘ በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ ተከፈተ። በዚሁ ማዕከል በኢሚግሬሽን፣በኢንቨስትመንት ፣ በማህበራዊ፣በልማትና በሌሎች ዘርፎች ዲያስፖራዎች ከመንግስት ተቋማት የሚፈልጓቸውን አገልግሎቶች የተመለከቱ መረጃዎችን ማግኘት ያስችላቸዋል ተብሏል። ዲያስፖራዎች በከተማዋ በሚቆዩባቸው ጊዜያት በማዕከሉ የበዓላትን ቀን ጨምሮ ከእሁድ እስከ እሁድ ባሉ ቀናት ከ2:00 ሰአት እስከ ምሽቱ 12:00 ሰዓት ድረስ በሁሉንም የአገልግሎት ዘርፎች መረጃዎችን ማግኘት እንደሚችሉ ተነግሯል።በተጨማሪም በከተማዋ የሚገኙና ዲያስፖራዎች ሊጎበኟቸው የሚፈልጓቸውን ነባርና አዳዲስ የልማት ስራዎችን እንዲሁም ሙዚዬሞችን ለመጎብኘት ሲያስቡ ቀድመው መረጃውን ለማግኘት የማዕከሉ መከፈት ፋይዳው የጎላ ነው ተብሏል።ዘገባው የፍስሐ ደሳለኝ ነው።

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 7696 ላይ ይላኩልን።

Telegram: https://t.me/ebstvworldwide

Follow us on: https://linktr.ee/ebstelevision

#ኢቢኤስ

#EBS