የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ተሳፋሪ እንዳይጭኑ እገዳ ተጣለ፡፡

የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ከአሽከርካሪዎች ውጭ ሌላ ተሳፋሪ እንዳይጭኑ እገዳ መጣሉን የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል።በአሁኑ ወቅት የዲያስፖራ አባላት ወደአገር እየገቡ ከመሆናችው ጋር ታይይዞ በከተማዋ የትራፊክ መጨናነቅ እና የዝርፊያ ምልክቶች እየታዩ መሆኑን ቢሮው እንደደረሰበት አስታውቋል። ስለሆነ ከታህሳስ 22/2014 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ከአሽከርካሪዎች ውጭ ሌላ ተሳፋሪ እንዳይጭኑ ቁጥጥር እንዲደረግና መመሪያውን በሚተላለፉት ላይም እርምጃ እንዲወሰድ ለሚመለከተው አካል የስራ ትዕዛዝ ማስተላለፉን ቢሮው ለአዲስ ነገር በላከው መግለጫ አሳውቋል፡፡ ቢሮው አክሎም በመዲናዋ በሞተር ብስክሌት ምክንያት የሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎችን እና ህገ ወጥ ድርጊቶችን መከላከል የሚያስችል የሞተር ብስክሌት ፈቃድና ቁጥጥር መመሪያ በማውጣት ወደ ስራ መገባቱንም አስታውሷል፡፡

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 7696 ላይ ይላኩልን።

Telegram: https://t.me/ebstvworldwide

Follow us on: https://linktr.ee/ebstelevision

#ኢቢኤስ#EBS