አዲስ ነገር – የተጭበረበሩት የአገራችን ባንኮች

ባለፉት 4 ዓመታት ብቻ በ155 የወንጀል መዛግብት ላይ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት ከ1 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር በላይ የሚሆን ገንዘብ በኢትዮጵያ ባንኮች ላይ የማጭበርበር ወንጀል መፈጸሙን የፍትህ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የማጭበርበር ወንጀል ሰለባ ሆነዋል ያላቸው የአገራችን ባንኮች 16 ሲሆኑ ከነዚህም 50 በመቶው ወይም ከ900 ሚሊየን ብር በላይ የማጭበርበር ወንጀል የተፈጸመው በመንግስታዊው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ ነው ብሏል፡፡
እንዲሁም 17 በመቶው ወይም 329 ሚሊየን ብር የሚጠጋው በአቢሲኒያ ባንክ ላይ ብሎም 8 ነጥብ 5 በመቶው ወይም 162 ሚሊየን ብሩ በኦሮሚያ ባንክ ላይ የተፈጸመ የማጭበርበር ወንጀል መሆኑን ነው ሚኒስቴሩ ያመለከተው፡፡
በባንኮቹ ላይ ወንጀሎቹ የተፈጸሙት ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም፣ በሀሰተኛ ሰነዶች፣ በይለፍ ቃል ስርቆት፣ በሞባይል ባንኪንግ፣ በሂሳብ ደብተርና በሀዋላ አገልግሎት በኩል መሆኑንም ነው የገለጸው፡፡
የፍትህ ሚኒስቴር ይህን የገለጸው በባንኮች ላይ የሚፈጸም የማጭበርበር ወንጀል መንስኤና የአፈፃጸም ዘዴን በመለየት የመፍትሄ ሃሳብ ለማቅረብ የሰራውን ጥናት ይፋ ባደረገበት ወቅት ሲሆን ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ በተካሄደው ጥናትም ከ370 ቢሊየን ብር በላይ በባንኮች ላይ የማጭበርበር ወንጀል ተሞክሮ ነበር ብሏል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New