18ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በነገው እለት በድምቀት የሚጀመር ይሆናል

18ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በነገው እለት በድምቀት የሚጀመር ይሆናል
1,972 አትሌቶች 192 ሀገራትን በመወከል ተሳታፊ የሚሆኑበት ይህ ሻምፒዮና ከፈረንጆቹ ሃምሌ 15 እስከ 24 በአሜሪካዋ ኦሪገን ግዛት ሂውጂን ከተማ የሚካሄድ ሲሆን በውድድሩ ተሳታፊ ከሆኑ ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ የመጀመሪያ አትሌቲክስ ቡድኗን ወደ ስፍራው መላኳ ይታወቃል::
ለ1 ወር ያህል ዝግጅት ሲያደርግ የቆየው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን በሻምፒዮናው ጥሩ ውጤት ያመጣሉ ተብለው በግምባር ቀደምትነት ከተቀመጡ ሀገራት መካከልም ይገኝበታል::
በሁለቱም ጾታዎች ስመ ጥር አትሌቶችን ያካተተችው ኢትዮጵያ ከመጪው አርብ ጀምሮ ውድድሯን የምታደርግ ሲሆን በመክፈቻው እለት አርብ ለሊት 9፤15 በ 3000 ሜትር መሰናክል ወንዶች ሃይለማርያም አማረ፣ጌትነት ዋለ እንደዚሁም ለሜቻ ግርማ በማጣርያው የሚሳተፉ ይሆናል በዚሁ ቀን ከለሊቱ 10፣10 በሴቶች 1500 ሜትር ሂሩት መሸሻ፣አክሱማይት እምባዬ እንዲሁም አያል ዳኛቸው የማጣርያ ውድድራቸውን ያደርጋሉ ተጠባቂው የ 10 ሺ ሜትር የሴቶች የፍጻሜ ውድድር ቅዳሜ ምሽት 4፤20 የሚካሄድ ሲሆን ለተሰንበት ግደይ፣ቦሰና ሙላቴ እና ግርማዊት ገብረ እግዚያብሄር ውድድሩን በበላይነት ለማጠናቀቀ ከሌሎች አትሌቶች ጋር የሚፎካከሩ ይሆናል::
ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በተካሄዱ 17 የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናዎች በሙሉ ተሳታፊ ስትሆን ከአንዱ በስተቀርም በሁሉም ሻምፒዮናዎች ላይ በሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ መግባት ችላለች እስካሁንም 85 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ከአለም 7ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች::
ጥሩነሽ ዲባባ እና ቀነኒሳ በቀለ 5 5 የወርቅ ሜዳሊያዎችን በመስብሰብ በቀዳሚነት ሲጠቀሱ እስካሁን ድረስ በተካሄዱ የአለም ሻምፒዮናዎች በሴቶች 14 የወርቅ 10 የብር እንዲሁም 14 የነሃስ በድምሩ 38 ሜዳሊያዎች ተመዝግበዋል በወንዶች 13 የወርቅ 15 የብርና 11 የነሃስ ሜዳሊያዎች ተገኝተዋል::

አዲስ ነገር / What’s New

EBSTV WRLDWIDE

EBSTV WRLDWIDE

EBS