የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ክለቦች ዝውውር

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ክለቦች በቀጣይ አመት ተጠናክረው ለመቅረብ በዝውውር መስኮቱ ንቁ ተሳትፎን እያደረጉ ይገኛሉ::
ከቀጣይ የውድድር አመት አንስቶ ስያሜውን ወደ መቻል እንደሚቀይር ይፋ ያደረገው መከላከያ አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ቡድኑን ለሁለት አመት እንዲረከብ ከስምምነት መድረሱ ተነግሯል፡፡
መከላከያ ከአሰልጣኝ ቅጥር በተጨማሪ በርካታ ተጫዋቾችን ማስፈረም የቻለ ሲሆን ከነዓን ማርክነህ ፣ በረከት ደስታ ፣ የሃዋሳ ከተማው ግብ ጠባቂ ዳግም ተፈራ፣ሳሙኤል ሳሊሶ፣ዳዊት ማሞ፣አሌክስ ተሰማ እና ምንይሉ ወንድሙ ክለቡን የተቀላቀሉ ተጨዋቾች ናቸው፡፡
የረመዳን የሱፍንና የቢኒያም በላይንና የዳዊት ተፈራን ዝውውር ያጠናቀቀው ቅዱስ ጊዮርጊስ የአቤል ያለውንና የሄኖክ አዱኛን ውል በይፋ አራዝሟል፡፡
የሽመክት ጉግሳ፣ሱራፌል ዳኛቸው እና በዛብህ መለዮን ጨምሮ የበርካታ ተጨዋቾችን ውል እያደሰ የሚገኘው ፋሲል ከነማ የባህርዳር ከተማውን ተከላካይ መናፍ አወልን የግሉ አድርጓል፡፡
በክረምቱ የዝውውር መስኮት በርካታ ተጨዋቾችን በመልቀቅ አዳዲስ ተጨዋቾችን እያስፈረመ የሚገኘው ኢትዮጵያ ቡና ራምኬል ጀምስትን ከጉለሌ ክፍለ ከተማ በማስፍረም በክረምቱ የዝውውር መስኮት ያስፈረማቸውን ተጫዋቾች 7 አድርሷል፡፡ አብዱልከሪም ወርቁ፣ብሩክ በየነ፣ጫላ ተሽታ፣መስፍን ታፈሰ፣ሃይለሚካኤል አደፍርስና አብዱልሃፊዝ ቶፊቅ ከዚህ ቀደም ለቡናማዎቹ ፊርማቸውን ያኖሩ ተጫዋቾች ናቸው፡፡
ድሬደዋ ከነማ ላለፉት ሁለት አመታት በመከላከያ እግርኳስ ክለብ ምክትል አሰልጣኝ የነበረውን ዮርዳኖስ አባይን በዋና አሰልጣኝነት መሾሙን ይፋ አድርጓል
ባህርዳር ከተማ በበኩሉ ሃብታሙ ታደሰን በማስፈረም በክረምቱ የዝውውር መስኮት ያስፈረማቸውን ተጨዋቾች ቁጥር 4 አድርሷል፡፡ ፍጹም ጥላሁን፣ዱሬሳ ሹቢሳ እና ያሬድ ባዬ ለጣና ሞገዶቹ ፊርማቸውን ያኖሩ ሌሎች ተጫዋቾች ናቸው፡፡
አርባምንጭ ከተማ እዮብ በቀታን የመጀመሪያው ፈራሚ ሲያደርግ ሲዳማ ቡና በበኩሉ ሙሉቀን አዲሱንና እንዳለ ከበደን ከ አዲስ አበባ ከተማ ማስፈረም ችሏል::

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

አዲስ ነገር / What’s New

EBSTV WRLDWIDE

EBSTV WRLDWIDE

EBS