አዲስ ነገር – የስንዴ ምርት በኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ በተያዘው አዲስ ዓመት ስንዴን ለውጪ ገበያ ለማቅረብ መቃረቧን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከፌደራል እና ከክልል ከፍተኛ ሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ወረዳዎች የስንዴ ኩታ ገጠም እርሻን ዛሬ በጎበኙበት ወቅት ነው እንዲህ ሲሉ የተናገሩት ።
በዚሁ ጊዜም በክልሉ ዱግዳ እና ቦራ ወረዳዎች የስንዴ ኩታ ገጠም እርሻ ላይ እየተከናወነ ያለው ስራ ተስፋ ሰጪ መሆኑንና በአዲሱ ዓመት ስንዴን ለውጪ ሀገር ገበያ ለማቅረብ ለተያዘው እቅድ መቅረብ መቻሉን የሚያሳይ ነው ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
መንግስት ከምሥራቅ ሸዋ ዞን ብቻ 7 ሚሊየን ኩንታል የስንዴ ምርት ለመሰብሰብ ማቀዱም ተሰምቷል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New