አዲስ ነገር – አዲሱ ስርዓተ ትምህርት

አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በሁሉም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በዛሬው ዕለት ተግባራዊ መደረግ ጀሞሯል፡፡

በመሆኑም አዲሱ ስርዓተ ትምህርት የሀገር በቀል ዕውቀትን ፣የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን እንዲሁም ተግባር ተኮር ትምህርትን ከስነምግባር ትምህርቶች ጋር አቀናጅቶ ለመስጠት እንዲያስችል ተደርጎ ተቀርጿል ነው የተባለው። ዛሬ በአዲስ አበባ የተጀመረው ስርዓተ ትምህርት ከቅድመ መደበኛ እስከ 8ኛ ክፍል ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን በ9ኛ እና 10ኛ ክፍል ደግሞ በሙከራ ደረጃ በተመረጡ 80 ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ እንደሚደረግ ሰምተናል። በልዩ ሁኔታ ዛሬ መስከረም 9 ቀን 2015 ዓ.ም ማስተማር የማይጀምሩ ትምህርት ቤቶች ተገቢው ክትትልና ድጋፍ ተደርጎላቸው ስራ እንደሚጀምሩም ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New