አዲስ ነገር – አጫጭር የዓለም መረጃዎች

#ሩሲያ

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለአገሪቱ 300 ሺ ተጠባባቂ ወታደሮች የግዳጅ ጥሪ አቀረቡ።ፕሬዝዳንቱ ጥሪውን ያቀረቡት በቴሌቪዥን የቀጥታ ስርጭት ባደረጉት ንግግር ነው። ፕሬዝዳንት ፑቲን የሀገራችንን ዳር ድንበር ለማስከበር በእጃችን ያለውን ሁሉ አማራጮች ልንጠቀም እንችላለን ሲሉ ማስጠንቀቃቸውን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል።

#ምዕራባዊያን አገራትሩሲያ ለተጠባባቂ ወታደሮቿ ጥሪ ማቅረቧን ተከትሎ ምዕራባዊያን አገራት ልዩ ልዩ ምላሾችን እየሰጡ መሆኑ ተሰምቷል።የብሪታንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የክሬምሊን መንግስትን አዲስ ውሳኔ በጥንቃቄ ልናየው ይገባል ሲል አሜሪካ በበኩሏ የወታደሮቹ የግዳጅ ጥሪ አንዱ የሩሲያ መንግስት የድክመት መገለጫ ነው ብላለች።የዩክሬን ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት ደግሞ ሩሲያ የጦርነቱ ሂደት ባሰበችው መልኩ ባለመሄዱ የዛሬውን ውሳኔ አሳልፋለች ሲል መንቀፉን አልጀዚራ ዘግቧል።

#ቱርክበባላንጣነት ሲተያዩ የነበሩት የቱርክ እና የእስራኤል መሪዎች ተገናኝተው መምከራቸው ተነግሯል።የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን እና የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ያር ላፒድ በመካሄድ ላይ ባለው የኒውዮርኩ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ነው በሀይል እና በመረጃ ደህንነት ጉዳዮች ላይ ምክክር ያደረጉት።እስራኤል እና ቱርክ ባለፈዉ ወር ዲፕሎሚሲያዊ ግንኙነታቸውን ዳግም ማስቀጠላቸውን አልጀዚራ በዘገባው አስታውሷል።

#ሴኔጋልየአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የሴኔጋሉ ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል በዚምባቡዌ ላይ የተጣለው ማዕቀብ እንዲነሳ ጠይቀዋል::ማኪ ሳል እየተካሄደ ባለዉ 77ኛው የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ በዚምባቡዌ ላይ የተጣለው ማዕቀብ የአገሪቱን ህዝብ ለከፋ ችግር የዳረገ በመሆኑ እንዲነሳ ጠይቀዋል።ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል አፍሪካ በቡድን 20 አገራት እንድትወከል ጭምር ጥሪ ማቅረባቸውን የዘገበው ቢቢሲ ነው።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New