አዲስ ነገር – የዓለም ውሎ

🇸🇾 ሶሪያ‼️ የአሸባሪው የአይ ኤስ ኤስ ድርጅት መሪ በሶሪያ ውጊያ ላይ እያለ መገደሉ ተነግሯል።የአሸባሪው የአይ ኤስ ኤስ ድርጅት ቁንጮ መሪው አቡ ሀሰን አል ሃሽሚ አል ኩራሺ በደቡባዊ ሶሪያ በውጊያ ላይ እያለ በሶርያ የነጻነት ተዋጊዎች መገደሉ ነው የተዘገበው።የአሜሪካ ማዕከላዊ እዝ ባወጣው መግለጫ የአሸባሪው የአይ ኤስ ኤስ መሪ መገደል ለድርጅቱ ታላቅ ሸንፈት እንደሆነ መግለፁን ፍራንስ ቱዌንቲ ፎር ዘግቧል።

🇷🇺 ሩሲያ ‼️ ሩሲያ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት “ኔቶ” አባል አገራት እና አሜሪካ በዩክሬን ጦርነት በቀጥታ ተሳትፎ እያደርጉ ነው አለች።የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ኔቶ እና ዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬን እያደርጉ ባሉት የጦር መሣሪያ ድጋፍ በዩክሬን ጦርነት በቀጥታ እየተሳተፉ ነው ብለዋል።ሚኒስትር ላቭሮቭ በዩክሬን ያሉ ሩሲያውያን ዜጎችን ከሞት ለመታደግ ስንል የአገሪቱን የሀይል መሰረተ ልማት እያሽመደመድን ነው ማለታቸውን ሬውተርስ ዘግቧል ።

🇩🇪 ጀርመን‼️ ጀርመን ዘመን አፈራሾቹን የአሜሪካ ስሪት ” የኤፍ 35 ” የጦር አውሮፕላኖች ግዢ ሂደት ልትፈፅም መሆኑ ተዘገበ።የጀርመኑ ቻንስለር ኦላፍ ሾልዝ የአገራችንን የመከላከያ ሀይል ለማጠናከር ስንል በአሜሪካው የሎኪድ ማርቲን ኩባኒያ የተመረቱትን የኤፍ 35 የጦር አውሮፕላኖች ግዢ በአውሮፓውኑ 2022 መጨረሻ ሙሉ ግዢው ይፈፀማል ብለዋል።እጅግ የረቀቁት የአሜሪካ የኤፍ 35 የጦር አውሮፕላኖች የኒውክለር ቦንብ የመተኮስ አቅም ያላቸው መሆኑን አር ቲ ዘግቧል።

🇺🇸 አሜሪካ‼️ በአሜሪካ የሳንፍራንሲስኮ ከተማ ፖሊሶች ገዳይ ሮቦቶች እንዲጠቀሙ ፈቃድ ልትሰጥ መሆኑ ተገለጸ።የሳንፍራንሲስኮ ከተማ አሰተዳደር የከተማዋ ፖሊሶች ገዳይ ሮቦቶችን መጠቀም እንዲችሉ ውሳኔ ማሳለፉን ነው ይፋ ያደረገው።የከተማዋ አንድ የፖሊስ ባለስልጣን ገዳይ ሮቦቶቹ አድማ መበተንን ጨምሮ አደገኛ ቦታዎችን ያለንን የፀጥታ ተደራሽነት ያሰፋሉ ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New