አዲስ ነገር – አጫጭር የዓለም መረጃዎች

🇺🇸#አሜሪካ አሜሪካ በሶሪያ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የአሸባሪው የአይ ኤስ ኤስ ድርጅት ሁለት ከፍተኛ አመራሮችን መግደሏን ይፋ አደረገች ::የአሜሪካ ማዕከላዊ ወታደራዊ እዝ በሶሪያ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የአይ ኤስ ኤስ ቡድን ሁለት አመራሮች በተፈፀማባቸው የአየር ጥቃት መገደላቸውን ነው ባወጣው መግለጫ ያስታወቀው።የማዕከላዊ ወታደራዊ እዙ ቃለ አቀባይ ጆ ቡሲኖ በአመራሮቹ ላይ የተወሰደው እርምጃ የአይ ኤስ ኤስ ድርጅት አቅምን በእጅጉ ያዳክማል ማለታቸውን ዩፒ አይ ዘግቧል ::

🇮🇷#ኢራንኢራን ፀረ መንግስት ተቃውሞ ውስጥ ተሳትፏል ያለችውን አንድ ሰልፈኛ በስቅላት ቀጣች ::ቴህራን “ማጂድሬሳ ራንሃርድ ” የተባለውን ሰልፈኛ በስቅላት እንዲቀጣ ስታደርግ አንድ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ነው የተዘገበው ።የኢራን የፍትህ ሚኒስቴር ግለሰቡ በስቅላት የተቀጣው 2 የኢራን የፀጥታ ኃይሎች ላይ ግድያ በመፈፀሙ እንደሆነ ማስታወቁን ዩፒ አይ ዘግቧል ::

🇺🇸#አሜሪካ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አሜሪካ ለዩክሬን የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋገጡ።የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባይደን ከዩክሬኑ አቻቸው ሾሎድሚር ዘለንስኪ ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት ኪይቭ ለሰላም ውይይት እያሳየች ያለውን ተነሳሽነት እንደሚያደንቁ ገልፀው ለዩክሬን የሚደረገው ድጋፍ ይቀጥላል ብለዋል ።ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ በበኩላቸው የወደሙ የሀይል መሰረተ ልማቶች ተጠግነው ወደ ስራ እንዲገቡ በሚደረገው ጥረት አሜሪካ ድጋፍ ታደርጋለች ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ መናገራቸውን ታይምስ ኦፍ እስራኤል ዘግቧል።

🇸🇸#ደቡብ ሱዳንየመንግስታቱ ድርጅት በደቡብ ሱዳን ባገረሸው ግጭት 40ሺ የሚጠጉ ዜጎች መፈናቀላቸውን አስታወቀ።በደቡብ ሱዳን በነዳጅ በበለፀገችው የአፐር ናይል ግዛት በተቀሰቀሰው ግጭት ወደ 40 ሺ የሚጠጉ ወገኖች ሲፈናቀሉ በግዛቲቱ የነበረው የሰብአዊ ድጋፍ እክል እንደገጠመው ነው ተመድ ያስታወቀው።በአፐር ናይል ግዛት በመንግስት ሀይሎች እና “ማይውት” በተሰኙት ታጣቂዎች ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ግጭት ይከሰት እንደነበር ቢቢሲ በዘገባው አስታውሷል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New