አዲስ ነገር – የዓለም ውሎ

🇺🇸#አሜሪካ አሜሪካ ለአፍሪካ አገራት የ 55 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ልታደርግ መሆኑ ተነገረ።የባይደን አስተዳደር ለአፍሪካ የሚያደርገውን ድጋፍ ያስታወቀው ዛሬ ከሚካሄደው የአሜሪካ አፍሪካ መሪዎች ጉባኤ አስቀድሞ መሆኑ ነው የተነገረው ።የአሜሪካ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪው ጃክ ሱሊቫን አሜሪካ የአፍሪካ ልማት ይፋጠን ዘንድ አስፈላጊውን ሁሉ እንደምታደርግ ተናግረዋል ።ፕሬዝዳንት ባይደን ከ50 የአፍሪካ መሪዎች ጋር ዛሬ እንደሚወያዩ ሲነገር ፕሬዝዳንቱ የአፍሪካ ህብረት በቡድን 20 መቀመጫ እንዲኖረው ድጋፍ ይሰጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ሬውተርስ ዘግቧል።

🇷🇺#ሩስያ ሩሲያ ወደ ውጭ ከምትልከው የነዳጅ ዘይት ምርት 89 ከመቶውን ወደ እስያ አገራት እየላከች መሆኑ ተሰምቷል።ክሬምሊን ወደ እስያ የምትልከው የነዳጅ ዘይት 89 ከመቶ መድረሱ የተገለፀው የአውሮፓ ህብረት ከሞስኮ የሚያስገባው የነዳጅ ዘይት በእጅጉ በቀነሰበት ጊዜ ነው ተብሏል።የሩሲያ የነዳጅ ዘይት ዋነኞቹ ሸማቶች ቻይና ፣ ህንድ እና ቱርክ መሆናቸውን አር ቲ ዘግቧል።

🇮🇷#ኢራን ኢራን በአውሮፓ ህብረት እና በብሪታንያ ላይ ማዕቀብ መጣሏን አስታወቀች።የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢራን ሁከት በማባባስ ተሳትፈዋል ባላችው የአውሮፓ ህብረት እና የብሪታንያ 9 ተቋማት እና 23 ባለስልጣናት ላይ ማዕቀብ መጣሉን አስታውቋል።የአውሮፓ ህብረት በቴህራን ላይ ማዕቀብ መጣሉን ተከትሎ ኢራን የአፀፋ ምላሽ ነው ያለችውን ማዕቀብ እንደጣለች የዘገበው አናዶሉ ነው።

🇾🇪#የመንየመንግስታቱ ድርጅት በጦርነት በደቀቀችው የመን ከ 3ሺ 7 መቶ በላይ ህፃናት መገደላቸውን አስታወቀ።ተመድ ላለፉት 7 አመታት በየመን በተካሄደው የርስ በርስ ጦርነት ከተገደሉት 3ሺ 7መቶ በላይ ህጻናት ባሻገር ከ 7 ሺ 2መቶ በላይ የሚሆኑት ህፃናት ለጉዳት መዳረጋቸውን ይፋ አድርጓል።በየመን 2.2 ሚሊየን ህፃናት ለከፋ የምግብ እጥረት ችግሮች እንደተዳረጉ ተመድ መግለፁን ኤፒ ዘግቧል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New