አዲስ ነገር – አጫጭር የዓለም መረጃዎች

#ኔቶ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት “ኔቶ” ለዩክሬን ተጨማሪ የጦር መሳሪያዎች ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪውን አቀረበ።የኔቶ ዋና ፀሐፊ ጄንስ ስቶልተንበርግ የአባል አገራትን ደህንነት ለማስጠበቅ እጅግ ጠቃሚ በመሆኑ አገራት ለዩክሬን የጦር መሳሪያዎች ድጋፍ እንዲያደርጉ በይፋ ጠይቀዋል ።ዋና ፀሐፊው ዩክሬን በአሁኑ ሰዓት የጦር መሳሪያዎች ድጋፍ የሚያሻት ጊዜ ላይ ነች ሲሉ መናገራቸውን ሬውተርስ ዘግቧል ።

🇨🇳#ቻይናቻይና ከአረብ አገራት ጋር ወታደራዊ ግንኙነት ልትመሰርት ማቀዷ ተዘገበ ።የቻይና የመከላከያ ሚኒስቴር የአለም ሰላምን ለማረጋገጥ ያለመ አዲስ የወታደራዊ ትብብር ከአረብ አገራት ጋር ለመመስረት ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል።ወታደራዊ ትብብሩ የቻይና -አረብ ግንኙነትን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያደርስ እንደሆነ መነገሩን አር ቲ ዘግቧል ።

🇮🇱#እስራኤልተመራጩ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታናያሁ ቃለ መሃላ ፈጸሙ።አንጋፋው ፖለቲከኛ ቤኒያሚን ኔታናያሁ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ቃለ መሃላ ሲፈፅሙ እስራኤልን ጠንካራ እና ተሰሚነት ያላት አገር ለማድረግ እሰራለሁ ብለዋል ።በኔታናያሁ አዲሱ ካቢኔ የወግ አጥባቂው የሊኩድ ፓርቲን ጨምሮ በርካታ የቀኝ ዘመም ፓርቲዎች መካተታቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል።

🇸🇸#ደቡብ ሱዳን በደቡብ ሱዳን በተከሰተው የጎሳ ግጭት ሳቢያ 30 ሺ ያክል ዜጎች መፈናቀላቸው ተሰማ።የመንግስታቱ ድርጅት በደቡብ ሱዳን የጆንግሊ ግዛት የተከሰተውን የጎሳ ግጭት ተከትሎ 30 ሺ ያክል የአገሪቱ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን አስታውቋል።የደቡብ ሱዳን መንግሥት በአገሪቱ በተደጋጋሚ የሚከሠተውን የጐሳ ግጭት በማስቆም የዜጐች መፈናቀል እና እንግልትን እንዲገታ ተመድ ጥሪ ማቅረቡን ሲጂቲኤን በዘገባው ገልጧል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New