አዲስ ነገር – አጫጭር የዓለም መረጃዎች

#ብራዚልተመራጩ የብራዚሉ ፕሬዚዳንት ሉላ ዳሲልቫ ቃለ መሃላ ፈጸሙ።ለ3ኛ የስልጣን ዘመን የብራዚል ፕሬዚዳንት ሆነው ቃለ መሃላ የፈፀሙት ሉላ ዳሲልቫ ህገ መንግስቱን በማስከበር የብራዚል ህዝብን ወደ አንድነት እንዲመጣ እሰራለሁ ብለዋል።ፕሬዚዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ የምርጫ ተፎካካሪያቸውን የቀድሞ የብራዚል ፕሬዚዳንት ጄየር ቦልሶናሮን ከ3 ወራት በፊት በተካሄደ ምርጫ ማሸነፋቸውን ዩፒአይ ዘግቧል።

#ዩክሬን ዩክሬን ባካሄደችው የሚሳኤል ጥቃት 4 መቶ ገደማ የሩሲያ ወታደሮችን መግደሏን አስታወቀች።የዩክሬን ባለስልጣናት በዶኔስክ ግዛት በአንድ የሩሲያ የጦር ሰፈር ላይ በፈፀሙት የሚሳኤል ጥቃት ከሞቱት በተጨማሪ 300 ያክል ወታደሮች መቁሰላቸውን አስታውቀዋል።ይሁንና ጥቃቱን አስመልክቶ የክሬምሊን መንግስት አንዳች መልስ ወይም ማስተባበያ አለመስጠቱን ቢቢሲ ዘግቧል ።

#ሩዋንዳየአውሮፓ ህብረት ሩዋንዳ በምስራቃዊው ኮንጎ ለሚንቀሳቀሰው የኤም 23 ታጣቂ ቡድን ድጋፍ ከመስጠት እንድትቆጠብ አሳሰበ።የህብረቱ የውጭ ግንኙነት ሀላፊ ጆሴፍ ቦሬል ኪጋሊ ለኤም 23 አማፂ ቡድን ድጋፏን በማቋረጥ ታጣቂ ቡድኑ በምስራቅ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ አሸማጋይነት ለተደረሰው ስምምምነት ተገዢ እንዲሆን ጥረት ማድረግ አለባት ብለዋል።የአውሮፓ ህብረት ፣ አሜሪካ እና የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከዚህ ቀደም ኪጋሊ ለኤም 23 የአማፂ ቡድን ድጋፍ እያደረገች ነው በሚል እንደሚወንጅሏት ቲአርቲ ዘግቧል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New