አዲስ ነገር – የትምህርት ሚኒስቴር ጥሪ

በውጭ አገራት በተለይም በአሜሪካ የምትገኙ ኢትዮጵያዊያን የመምህራንን አቅም የሚያጎለብቱ ስልጠናዎችን በመስጠት ለትምህርት ዘርፉ ድጋፍ እንድታደርጉ ሲል የትምህርት ሚኒስቴር ጥሪ አቅርቧል፡፡ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይህንን ጥሪ ያቀረበው ኢትዮጵያ 2050 የተባለውና በአሜሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አማካኝነት የተቋቋመው ግብረ-ኃይል አሰናድቶት በነበረ የውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡ በትምህርት ጥራትና የልሕቀት ማዕከላትን ማሻሻል ላይ አተኩሮ በተመከረበት መድረክ ላይ የትምህርት ሚኒስቴር ሰፊ የመምህራን ክፍተት እንዳለ በመጠቆም የሚፈለገው በውጭ ያሉ ኢትዮጵያዊያን መምህራኖቻችን ለዶክትሬት ትምህርት ወደውጭ አገር እንዲጓዙ እንድታግዙ ሳይሆን በስራ ላይ እያሉ ጥሩ መምህራን እንዲሆኑ እንድትረዷቸው ነው ብሏል፡፡ለዚህም አቅማቸውን ለማጎልበት የሚሆኑ አጫጭር ስልጠናዎችን እንዲያገኙ ብታመቻቹ ሲል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የጠየቀ ሲሆን ግብረ ኃይሉም በተማሪዎች አቅም ዙሪያ ያደረኩትን ጥናት ተመርኩዤ እየሰራሁ ከምገኘው ስራ ጎን ለጎን በመምህራን አቅም ላይም የሚጠበቅብኝን አደርጋለሁ ብሏል፡፡የሀገራችንን የትምህርት ጥራትና የልሕቀት ማዕከላትን ደረጃ ለማሻሻል የሚሰራ የባለሙያዎች ቡድን በማቋቋም ስሰራ ቆይቻለሁ ያለው ኢትዮጵያ 2050 ግብረ ኃይል የዛሬ 4 ዓመት ገደማ ነበር በአሜሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን አማካኝነት የተቋቋመው፡፡ ዘነበ ኃይሉ እንደዘገበው፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New