አዲስ ነገር – አጫጭር የዓለም መረጃዎች

#ብራዚል

ብራዚል የአገሪቱን ፓርላማ ጥሰው በመግባት ሁከት የፈጠሩ ነውጠኞች ላይ እርምጃ እንደምትወስድ አስታውቃለች።የብራዚሉ ፕሬዚዳንት ሉላ ዳሲልቫ የቀድሞ የአገሪቱ መሪ ጄየር ቦልሶናሮ ደጋፊዎች በሆኑት በነዚሁ ነውጠኞች ላይ መንግስት ጠንከር ያለ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቀዋል ።ነውጠኞቹ በአገሪቱ ፓርላማ እና ጠቅላይ ፍ/ቤት ጥሰው በመግባት ችግር መፍጠራቸው ሲነገር የአገሪቱ ፖሊስ በርካታ ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋል መጀመሩን ነው ቢቢሲ የዘገበው ።

#ዩክሬን

ዩክሬን ሩሲያ 600 የዩክሬን ወታደሮች ገድያለሁ ማለቷን ሀሰት ነው ስትል አስተባበለች።የዩክሬን የመከላከያ ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ ሞስኮ ያለአንዳች ማስረጃ 600 የኪይቭ ወታደሮች ገድያለሁ በሚል ያሰራጨችው መረጃ ተራ ፕሮፓጋንዳ ነው ሲሉ አጣጥለዋል።ሩሲያ በሁለት ህንፃዎች ላይ በነበሩ በሺዎች በሚቆጠሩ የዩክሬን ወታደሮች ላይ በወሰደችው የአፀፋ ጥቃት 600 ወታደሮችን እንደገደለች ትናንት ማስታወቋን ቢቢሲ በዘገባው አስታውሷል።

#ቻይና

ቻይና በአገሪቱ ባገረሸው የኮሮና ወረርሽኝ ከ 88 ሚሊየን የሚበልጡ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን አስታወቀች።በቻይናዋ የሄናን ግዛት በተሰራጨው የኮሮና ወረርሽኝ ከግዛቲቱ አጠቃላይ ነዋሪዎች 90 ከመቶ የሚጠጉት በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር ሀላፊዎች ተናግረዋል።በግዛቲቱ በተስፋፋው የኮሮና ወረርሽኝ ሳቢያ በርካታ ህሙማን ወደ ጤና ተቋማት መጉረፋቸውን ተከትሎ ተቋሟቱ ከመጠን በላይ ተጨናንቀዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል ::

#ሱዳን

የመንግስታቱ ድርጅት በሱዳን የወታደራዊ መንግስቱ አመራሮች እና የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሚካሄደውን ውይይት በይፋ አስጀመረ።ተመድ ባወጣው መግለጫ ለሁለተኛ ጊዜ በሱዳን የተጀመረው ውይይቱ ለ 4ቀናት የሚካሄድ ሲሆን በጉባኤው የሱዳን ወታደራዊ መሪዎችን ጨምሮ በርካታ ፓርቲዎች መሳተፋቸውን አስታውቋል።በተመድ አመቻችነት የሚካሄደው ውይይት በአገሪቱ ያለውን የፖለቲካ ቀውስ መፍትሔ እንዲበጅለት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል መባሉን ቢቢሲ ዘግቧል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New