አዲስ ነገር – ሳኡዲ አረቢያ በሃጅ እና ኡምራ ተጓዦች እና ሌሎችም መረጃዎች

🇧🇷ብራዚል

በብራዚል በድህረ ምርጫ ተቃውሞ ላይ ተሳትፈዋል የተባሉ 1ሺ 5 መቶ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጄየር ቦልሶናሮ ደጋፊዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል፡፡ሁከቱ የተቀሰቀሰው ቦልሶናሮ በምርጫው መሸነፋቸውን አለመቀበላቸውን ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎቻቸው ባስነሱት መጠነ ሰፊ ተቃውሞ ሲሆን የብራዚሉ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ሉላዳ ሲልቫ የቦልሶናሮ ደጋፊዎችን መፈንቅለ መንግስት ናፋቂዎችና “የሽብር ተግባር ፈፃሚዎች” ሲሉ ማውገዛቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

🇨🇳ቻይና

ቻይና ከደቡብ ኮሪያ እና ጃፓን ወደ አገሯ ለሚገቡ ተጓዦች ቪዛ እንደማትሰጥ አስታውቃለች።ቤጂንግ ለተጓዦቹ ቪዛ መከልከሏን ያስታወቀችው አገራቱ በቻይና መንገደኞች ላይ ገደብ በመጣላቸው ነው ተብሏል፡፡ቤጂንግ በቻይና መንገደኞች ላይ ያልተገባ ክልከላ በሚጥሉ አገራት ላይ የአፀፋ እርምጃ እንደምትወስድ ከዚህ ቀደም ማስጠንቀቋን ቢቢሲ በዘገባው አስታውሷል።

🇸🇦ሳኡዲ አረቢያ

ሳኡዲ አረቢያ በሃጅ እና ኡምራ ተጓዦች ላይ ለ3 አመታት ጥላው የነበረውን ገደብ አነሳች ።የሳኡዲ አረቢያ መንግስት የኮሮና ወረርሽኝ ለመከላከል በሚል ወደ አገሪቱ የሚገቡ የሀጅ እና ኡምራ ተጓዦች ቁጥር የሚገድበውን ህግ ሙሉ በሙሉ ማንሳቱን አስታውቋል።ሪያድ ገደቡን ማንሳቷን ተከትሎ ወደ አገሪቱ የሚገቡ ጉብኚዎች ቁጥር ኮሮና ከመከሠቱ በፊት ወደነበረው አሀዝ እንደሚመለስ ፍራንስ ቱዌንቲ ፎር ዘግቧል ።

🇷🇼ሩዋንዳ

ሩዋንዳ የዴሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐብሊክ ተፈናቃዮችን እንደማትቀበል ይፋ አደረገች።የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ኪጋሊ በምስራቃዊው ኮንጎ በቀጠለው ግጭት አንዳችም እጇ የሌለበት በመሆኑ ከአገሪቱ የሚመጡ ስደተኞችን አንቀበልም ብለዋል ።ፕሬዚዳንት ካጋሜ የምስራቃዊው ኮንጎ ግጭትን አስመልክቶ የአለም አገራት ተገቢ አረዳድ የላቸውም ሲሉ መውቀሳቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New