LatestNews

የህዳሴ ግድብን የተመለከተው የሶስትዮሽ ስብሰባ የአፍሪካ ህብረት በጨመራቸው ባለሙያዎች ሚና ላይ ተወያየ

የህዳሴ ግድብን የተመለከተው የሶስትዮሽ ስብሰባ የአፍሪካ ህብረት በጨመራቸው ባለሙያዎች ሚና ላይ ውይይት አድርጓል።

የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር በበይነ መረብ በኢትዮጵያ ግብፅና ሱዳን የውሃ ሚኒስትሮች መካከል የተካሄደውን ውይይት አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።

በመግለጫው ላይ የቀጣይ የድርድር ሂደትና የጊዜ ሰሌዳ የውይይቱ ዋነኛ አጀንዳ እንደነበር አስታውቋል።

በውይይቱ ከሶስቱም ሀገራት ሁለት ሁለት ባለሙያዎች በመመደብ በቀጣይ ህብረቱ በሰየማቸው ባለሙያዎች ተጨማሪ ሚና ዙሪያ ተወያይተው ለውሃ ሚኒስትሮች እንዲያቀርቡ ከስምምነት መደረሱን ጠቅሷል።