ለቲቢ በሽታ አዲስ መድሃኒት
የደቡብ አፍሪካው ዴዝሞንድ ቱቱ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች መድኃኒት ለተላመደ የቲቢ በሽታ ፍቱን መድኃኒት ማግኘታቸውን አስታወቁ።
ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት ባካሄዷቸው ሙከራዎች ያገኙት መድኃኒት የተላመደ የልጆችንም ሆነ አዋቂ የቲቢ በሽታ በማከም በእጅጉ ፍቱን ነው።
“ሌሾፍሎክሲን ” የተባለው መድሃኒት በተለይ ከ6 ወር በላይ ላሉ ሕፃናት በየቀኑ አንድ ክኒን የሚሰጥ ሲሆን መድሃኒቱ በሕፃናቱ ላይ የሚያደርሰው ምንም ጉዳት የለም ብለዋል።
በዓለማችን በየዓመቱ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በመድሃኒት በማይድነው የቲቢ በሽታ የሚጠቁ ሲሆን ህመሙን ለመፈወስ ከማስቸገሩ በተጨማሪም ወጭው እጅግ ከፍተኛ ነው። በደቡብ አፍሪካው የመድሃኒት ሙከራ ለማይድነው የቫይረስ አይነት ከተጋለጡ 453 ሕፃናት መካከል አምስቱ ብቻ በበሽታው መያዛቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።