GeneralNews

ሞባይል ስልኮችን አብዝቶ መጠቀም ለጭንቅላት ካንሰር ይዳርጋልን???

ሞባይልን አብዝቶ በመጠቀም የሚፈጠረው ጨረር ተጠቃሚዎችን ለጭንቅላት ካንስር ይዳርጋል ሲሉ በርካቶች ሲናገሩ ይሰማል።
ይሁን እንጂ ከዓለም የጤና ድርጅት ጋር በቅንጅት የተሰራ አንድ ጥናት ይፋ እንዳደረገው ሞባይል ስልኮችን አብዝቶ መጠቀም ብቻዉን ለጭንቅላት ካንሰር እንደማያጋልጥ አስታውቋል።

ለ7 ዓመታት ተደርጓል የተባለው ይህ ጥናት ከ250 ሺህ በላይ በጎ ፈቃደኞች የተሳተፉበት ሲሆን የጭንቅላት ካንሰር እና ሞባይል ስልክ ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌላቸው እና ሞባይል ስልክ አብዝተው የሚጠቀሙ እና አልፎ አልፎ የሚጠቀሙ ሰዎች ላይም ምንም አይነት ልዩነት እንደሌለ አረጋግጫለሁ ማለቱን የዘገበው ኤቢሲ ኒውስ ነው።